Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተ​ውም በር መጣ፤ በሰ​ባ​ቱም ደረ​ጃ​ዎች ላይ ወጣ፤ በበሩ በኩል ያለ​ው​ንም የመ​ድ​ረ​ኩን ወለል ወር​ዱን አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ ደረጃዎቹን ወጥቶ የበሩን መግቢያ መድረክ ለካ፤ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚያም በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው የቅጽር በር አልፎ ሄደ፤ ደረጃውንም ወጥቶ ከጫፉ የመድረኩን ወለል ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር መጣ በደረጃዎቹም ላይ ወጣ፥ በበሩ በኩል ያለውንም የመድረኩን ወለል ወርዱን አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:6
24 Referencias Cruzadas  

የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ጓዳ​ዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠ​ገብ ነበረ። ከዚ​ያም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው ደርብ፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ወደ ሦስ​ተ​ኛው ደርብ የሚ​ወ​ጡ​በት መውጫ ነበ​ረው።


እስ​ከ​ዛ​ሬም ድረስ በን​ጉሥ በር በም​ሥ​ራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረ​ኞች ነበሩ።


በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ኖች፥ በም​ሥ​ራቅ፥ በም​ዕ​ራብ፥ በሰ​ሜን፥ በደ​ቡብ በሮች ነበሩ።


ከዚ​ያም በኋላ የሄ​ሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አን​ጻር ያለ​ውን ሠራ። ከእ​ር​ሱም በኋላ የም​ሥ​ራቁ በር ጠባቂ የሴ​ኬ​ንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።


ይቅ​ር​ታና ቅን​ነት ተገ​ናኙ፤ ጽድ​ቅና ሰላም ተስ​ማሙ።


በከ​ር​ሲት በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ ወዳ​ለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፥ በዚ​ያም የም​ነ​ግ​ር​ህን ቃል አን​ብብ፤ እን​ዲ​ህም በል፦


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ከቤቱ መድ​ረክ ላይ ወጥቶ በኪ​ሩ​ቤል ላይ ተቀ​መጠ።


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ጻር ወደ​ሚ​ያ​ሳ​የው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ወሰ​ደኝ። እነ​ሆም በበሩ መግ​ቢያ ሃያ አም​ስት ሰዎች ነበሩ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች የዓ​ዙ​ርን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥ​ያን አየሁ።


ወደ ሰሜ​ንም መራኝ፤ እነ​ሆም በው​ጭው አደ​ባ​ባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንና ወር​ዱ​ንም ለካ።


መስ​ኮ​ቶ​ቹም፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ የዘ​ን​ባባ ዛፎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ እን​ደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ።


ወደ ደቡ​ብም መራኝ፤ እነ​ሆም ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ የግ​ን​ቡን አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም እን​ደ​ዚ​ያው መጠን አድ​ርጎ ለካ።


ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ አንዱ በዚህ አን​ዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


እነ​ሆም በቤቱ ውጭ በዙ​ሪ​ያው ቅጥር ነበረ፤ በሰ​ው​የ​ውም እጅ የክ​ንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድ​ስት ክንድ ያለ​በት የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅ​ጥ​ሩ​ንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመ​ቱ​ንም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ።


የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤


ውስ​ጠ​ኛ​ው​ንም ቤት ለክቶ በፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር መን​ገድ አወ​ጣኝ፤ እር​ሱ​ንም ዙሪ​ያ​ውን ለካው።


ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አመ​ጣኝ።


የእ​ር​ከ​ኑም ርዝ​መት ዐሥራ አራት ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፤ አራ​ቱም መዐ​ዝን ትክ​ክል ነው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ያለው ክፈፍ የክ​ንድ እኩ​ሌታ ነው፤ መሠ​ረ​ቱም በዙ​ሪ​ያው አንድ ክንድ ነው፤ ደረ​ጃ​ዎ​ቹም ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከ​ታሉ።”


መድ​ረ​ካ​ቸ​ውን በመ​ድ​ረኬ አጠ​ገብ፥ መቃ​ና​ቸ​ው​ንም በመ​ቃኔ አጠ​ገብ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና። በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠ​ሩ​ትም ርኵ​ሰት ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ፤ ስለ​ዚህ በቍ​ጣዬ አጠ​ፋ​ኋ​ቸው።


ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅ​ደሱ በር መለ​ሰኝ፤ ተዘ​ግ​ቶም ነበር።


አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።


ወደ መቅ​ደ​ሱም መዝ​ጊያ መለ​ሰኝ፤ እነ​ሆም ውኃ ከቤቱ መድ​ረክ በታች ወደ ምሥ​ራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥ​ራቅ ይመ​ለ​ከት ነበ​ርና፤ ውኃ​ውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመ​ሠ​ዊ​ያው በደ​ቡብ በኩል ይወ​ርድ ነበር።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos