Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነ​ሆም በቤቱ ውጭ በዙ​ሪ​ያው ቅጥር ነበረ፤ በሰ​ው​የ​ውም እጅ የክ​ንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድ​ስት ክንድ ያለ​በት የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅ​ጥ​ሩ​ንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመ​ቱ​ንም አንድ ዘንግ አድ​ርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የቤተ መቅደሱን ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የከበበ ቅጥር አየሁ፤ በሰውየውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ መለኪያ ዘንግ አየሁ፤ እያንዳንዱ ክንድ፣ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበር፤ እርሱም ቅጥሩን ለካው፤ ስፋቱ አንድ መለኪያ ዘንግ ሲሆን፣ ቁመቱም እንዲሁ አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነሆ፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ያለው የመለኪያው ዘንግ ርዝመት አንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ ስድስት ክንድ ነበረ፤ ቅጥሩንም ለካ፥ ስፋቱ አንድ ዘንግ፥ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ቅጥር ነበረ፤ በሰውዬው እጅ ያለው መለኪያ ዘንግ በእርሱ ረጃጅም ክንዶች ስድስት ይሆናል፤ የቅጽሩ ስፋት ሲለካ አንድ ዘንግ፥ ከፍታው ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ። የእርሱ ክንድ ግን በሌሎች ሰዎች ክንድ ሲለካ አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆም፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ የክንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድስት ክንድ ያለበት የመለኪያ ዘንግ ነበረ፥ የቅጥሩንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:5
10 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያን ጊዜ አፋ​ችን ደስ​ታን ሞላ፥ አን​ደ​በ​ታ​ች​ንም ሐሤ​ትን አደ​ረገ፤ በዚ​ያን ጊዜ አሕ​ዛብ፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገ​ርን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው” አሉ።


በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን።


እን​ግ​ዲህ በም​ድ​ርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳ​ር​ቻ​ሽም ውስጥ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ አይ​ሰ​ማም፤ ቅጥ​ሮ​ችሽ ድኅ​ነት ይባ​ላሉ፤ በሮ​ች​ሽም በጥ​ርብ ድን​ጋይ ይሠ​ራሉ።


ለመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍ ያለ ወለል በዙ​ሪ​ያው እን​ዳ​ለው አየሁ፤ የጓ​ዳ​ዎ​ቹም መሠ​ረት ቁመቱ ሙሉ ዘንግ የሚ​ያ​ህል ስድ​ስት ክንድ ነበረ።


ውስ​ጠ​ኛ​ው​ንም ቤት ለክቶ በፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር መን​ገድ አወ​ጣኝ፤ እር​ሱ​ንም ዙሪ​ያ​ውን ለካው።


በአ​ራ​ቱም ወገን ለካ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ያል​ተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ይለይ ዘንድ ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙ​ሪ​ያው ነበረ።


የመ​ሠ​ዊ​ያው ልክ በክ​ንድ ይህ ነው፤ ክን​ዱም ክንድ ተጋት ነው። የመ​ሠ​ረ​ቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስን​ዝ​ርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙ​ሪ​ያው አለ፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው ቁመት እን​ዲሁ ነው።


እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos