Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እነሆ በፍሬያማው የእርሻ ቦታ አንድ እንኳ ደስተኛ የለም፤ በወይን ተክል ቦታዎች የእልልታና የዝማሬ ድምፅ አይሰማም፤ የወይን ጠጅ ለመጥመቅ የወይን ፍሬ የሚጨምቅ የለም፤ እግዚአብሔር የደስታ እልልታን ሁሉ እንዲቆም አድርጎአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ደስ​ታና ሐሤ​ትም ከወ​ይን ቦታሽ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ በወ​ይ​ን​ሽም ቦታ​ዎች ፈጽ​መው ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም፤ በመ​ጥ​መ​ቂ​ያ​ውም ወይ​ንን አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ረጋ​ጮ​ቹን አጥ​ፍ​ቻ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፥ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፥ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፥ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 16:10
13 Referencias Cruzadas  

በክፉ ሰዎች የአትክልት ቦታ ከወይራ ፍሬ ዘይት ያወጣሉ፤ ከወይን ዘለላም የወይን ጠጅን ይጠምቃሉ፤ እነርሱ ግን ይጠማሉ።


ዳግመኛ የወይን ጠጅ ስለማይገኝ ሰዎች በየአደባባዩ ይጮኻሉ፤ ደስታ ለዘለዓለም ጠፍቶአል፤ ሐሴትም በምድር ላይ አይገኝም፤


እናንተ በኑሮአችሁ የተማመናችሁ ሴቶች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተስፋ የሚያስቈርጥ ጭንቀት ይደርስባችኋል፤ ከወይንም ሆነ ከሌላው ተክል ሁሉ በቂ ፍሬ አታገኙም።


ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም።


በምድሪቱ የምትኖሩ ሕዝብ ሁሉ የመጥፊያችሁ ጊዜ ደርሶአል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ እርሱም የሁከት ቀን ነው እንጂ በከፍተኛ ቦታዎች የመፈንጠዣ ቀን አይደለም።


የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል።


ድኾችን ጨቊናችሁ፤ እህላቸውንም አስገብራችሁ፤ ከጥርብ ድንጋይ ቤቶች ሠርታችኋል፤ እናንተ ግን አትኖሩባቸውም፤ የሚያስደስት ወይን ተክላችኋል፤ ነገር ግን ከእርሱ የሚገኘውን የወይን ጠጅ እናንተ አትጠጡም።


በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ለቅሶ ይሆናል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እኔ በመካከላችሁ ስለማልፍ ነው፤” ይህንንም የተናገረ እግዚአብሔር ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእህል ሰብል አጫጆች አጭደው ሳይጨርሱ፥ አራሾች የሚደርሱባቸውና ወይን ጨማቂዎችም የወይን ፍሬ ጨምቀው ሳይጨርሱ፥ የወይን ተካዮች የሚደርሱባቸው ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ተራራዎች ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያፈልቃሉ፤ ኰረብቶችም በወይን ጠጅ ይጥለቀለቃሉ።


ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”


ሁሉም ወደ ወይን ተክሎቻቸው ወጥተው የወይን ፍሬ ለቀሙ፤ የወይን ጠጅ ጠምቀው ትልቅ በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም መቅደስ ገብተው በዚያ እየበሉና እየጠጡ ስለ አቤሜሌክ በማፌዝ ተናገሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos