Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ጌታው የእግዚአብሔር አገልጋዮች ወደ ሆኑ ፈራጆች ዘንድ ይውሰደው፤ እዚያም ከበር ወይም ከበር መቃን አጠገብ አቁሞ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜ ልኩ ድረስ ባርያ ሆኖ ያገልግለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ጌታው ወደ ዳኞች ይውሰደው፤ ወደ በር ወይም ወደ በሩ መቃን ወስዶ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም ዕድሜ ዘመኑን የርሱ አገልጋይ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታው ወደ እግዚአብሔር ያቅርበው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ያገልግለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘላለምም ባሪያው ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 21:6
24 Referencias Cruzadas  

ሽማግሌዎቹም “ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸውና ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብትሰጣቸው፥ እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል” ሲሉ መለሱለት።


እግዚአብሔር በሰማያዊው ጉባኤ አማልክት ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ በመካከላቸው ተገኝቶ ፍርድ ይሰጣል፦


“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


“ሁለት ሰዎች ሲጣሉ አንዲት ነፍሰ ጡር መተው ቢያስወርዳትና ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስባት ቢቀር፥ ያ ጒዳት ያደረሰባት ሰው የሴቲቱ ባል የሚጠይቀውን ያኽል ካሣ ይክፈል፤ ይህም የሚከፍለው ካሣ መጠን በዳኞች የጸደቀ ይሁን።


ባሪያው ግን ‘ጌታዬን፥ ሚስቴንና ልጆቼን እወዳለሁ’ ብሎ ነጻ መውጣት ባይፈልግ፥


“አንድ ሰው ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች ነጻ አትውጣ፤


“በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል አትናገር፤ የሕዝብህንም መሪ አትስደብ።


ቀድሞ የነበሩሽን ዐይነት ገዢዎችንና አማካሪዎችን አስነሣልሻለሁ፤ ከዚህ በኋላ ‘እውነት የሚገኝባት ታማኝ ከተማ’ ተብለሽ ትጠሪአለሽ።”


“ምድሪቱ ለዘለቄታ መሸጥ አይገባትም፤ እርስዋ የእኔ እንጂ የእናንተ አይደለችም፤ እናንተ እንደ መጻተኛ ሆናችሁ እንድትጠቀሙባት ብቻ ፈቅጃለሁ።


እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ እያገለገለህ እንደ መጻተኛ ይኑር፤


መሪዎችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙትን ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኲላዎች ናቸው።


“በዚያን ጊዜ እነርሱን እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤ ‘በሕዝባችሁ መካከል የሚነሣውን የጠብና የክርክር አቤቱታ አድምጡ፤ በራሳችሁ ሕዝብ ወይም በእናንተ ውስጥ በሚኖሩት መጻተኞች መካከል ስለሚነሣው ጠብና ክርክር ሁሉ በትክክል ፍረዱ።


“ነገር ግን ባሪያህ አንተንና ቤተሰብህን በመውደዱና ከአንተም ጋር ስምምነት ስላለው ለመሄድ አይፈልግም ይሆናል፤


ይህም ከሆነ ወደ ቤትህ ደጃፍ ወስደህ ጆሮውን በወስፌ ብሳው፤ ከዚያም በኋላ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ የአንተ ባሪያ ይሆናል፤ ለሴት ባሪያህም ቢሆን ይህንኑ አድርግ።


“አምላክህ እግዚአብሔር ለየነገድህ በሚሰጠው ምድር በእያንዳንዱ ከተማ ዳኞችና ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ትሾማለህ፤ እነዚህም ሰዎች ለሕዝቡ ያለ አድልዎ መፍረድ ይገባቸዋል፤


“ልጄ ጡት በሚተውበት ጊዜ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ወደሚኖርበት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወዲያውኑ እወስደዋለሁ” ብላ ለባልዋ ነግራው ስለ ነበር ሐና በዚህ ጊዜ አብራ አልወጣችም፤


አኪሽ ግን ዳዊትን ስለሚተማመንበት በልቡ “በወገኖቹ በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ የተጠላ ስለ ሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያገለግለኛል” በማለት ያስብ ነበር።


ዳዊትም “እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የማደርገውንም አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ” ሲል መለሰለት። አኪሽም “መልካም ነው! እኔ አንተን ለዘለቄታ የራሴ የክብር ዘብ አደርግሃለሁ!” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos