መዝሙር 133 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዝሙር 133የመዓርግ መዝሙር።1 በእግዚአብሔር ቤት፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ። 2 በሌሊት በቤተ መቅደስ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም አመስግኑት። 3 ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ። |