መዝሙር 130 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዝሙር 130የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።1 አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዐይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ፤ ከትልልቆች ጋር፥ ከእኔም ይልቅ ከሚከብሩ ጋር አልሄድሁም። 2 ራሴን አዋረድሁ እንጂ። ለነፍሴ ዋጋዋን ትሰጣት ዘንድ፤ የእናቱንም ጡት እንዳስጣሉት በቃሌ ጮኽሁ። 3 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመናል። |