La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 61 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 61

የመማጠኛ ጸሎት

1 አምላክ ሆይ! ጩኸቴን አድምጥ፤ ጸሎቴንም ስማ።

2 ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።

3 አንተ ጠባቂዬና ከጠላቶቼ የምከለልብህ ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።

4 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በቤትህ እንድኖርና በጥበቃህ ሥር መጠለያ እንዳገኝ ፍቀድልኝ።

5 አምላክ ሆይ! ስእለቴን ሰማህ፤ አንተን ለሚፈሩ ሰዎች ያዘጋጀኸውን በረከት ለእኔም ሰጠኸኝ።

6 በንጉሡ ዕድሜ ላይ ብዙ ዓመቶች ጨምርለት፤ ለብዙ ዘመንም እንዲኖር አድርገው!

7 አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤ በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።

8 ለአንተ የተሳልኩትን በየቀኑ በማቅረብ ዘወትር የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia