La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 2

በእግዚአብሔር የተመረጠ ንጉሥ

1 አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?

2 እግዚአብሔርንና መሲሑን ለመቃወም የዓለም ነገሥታት ተነሣሡ፤ ሹሞቻቸውም ከእነርሱ ጋር ተባበሩ።

3 “እግር ብረታቸውን ከእግራችን እንቊረጥ፤ ገመዳቸውን በጥሰን እንጣል” አሉ።

4 በሰማይ ዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ይስቅባቸዋል፤ በከንቱ ሐሳባቸውም ጌታ ያፌዝባቸዋል።

5 ከዚህ በኋላ በቊጣው ይገሥጻቸዋል፤ በመዓቱም ያስፈራራቸዋል።

6 “በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ ንጉሤን ሾምኩ” ይላቸዋል።

7 “የእግዚአብሔርን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤

8 ለምነኝ፤ አሕዛብ ሁሉ እንዲገዙልህ አደርጋለሁ፤ ምድርም በሙሉ የአንተ ርስት ትሆናለች።

9 በብረት በትር ትሰብራቸዋለህ፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ቀጥቅጠህ ታደቃቸዋለህ’ ” አለኝ።

10 እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤ እናንተ የምድር ገዢዎች ተጠንቀቁ።

11 እግዚአብሔርን በፍርሃት አገልግሉት፤ በመንቀጥቀጥም ተገዙለት።

12 ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ በመንቀጥቀጥ ስገዱለት እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia