La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 16

የእግዚአብሔርን አለኝታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

1 አምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤

2 እግዚአብሔርን “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ያለኝ መልካም ነገር ሁሉ ያንተ ስጦታ ነው” አልኩት።

3 በምድር ላይ የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም እደሰታለሁ።

4 ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።

5 እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።

6 ለእኔ የተለኩልኝ የድንበር መስመሮች ያረፉት በሚያስደስቱ ቦታዎች ላይ ነው፤ በእርግጥ እኔ የሚያስደስት ርስት አለኝ።

7 የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል።

8 ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።

9 ስለዚህ ልቤ ተደስቶ ይፈነጥዛል፤ ሰውነቴም ያለ ስጋት ያርፋል።

10 ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም።

11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia