La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 13

ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

1 እግዚአብሔር ሆይ፥ እስከ መቼ ትረሳኛለህ? የምትረሳኝ ለዘለዓለም ነውን? እስከ መቼስ ከእኔ ትሰወራለህ?

2 ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል? እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል? እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?

3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤ የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ ብርታቱን ስጠኝ።

4 ጠላቶቼ “አሸነፍነው” ብለው እንዲመኩ፥ በእኔም መውደቅ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።

5 እኔ በማያቋርጥ ፍቅርህ እተማመናለሁ፤ በማዳንህ እደሰታለሁ።

6 እግዚአብሔር ሆይ! በጎ ነገር ስላደረግህልኝ ለአንተ እዘምራለሁ።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia