La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 128 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 128

ለእግዚአብሔር በመታዘዝ የሚገኝ በረከት

1 እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው።

2 ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።

3 ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤ ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ።

4 እግዚአብሔርን የሚፈራ እንደዚህ የተባረከ ይሆናል።

5 እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ! የኢየሩሳሌምን ብልጽግና በሕይወትህ ዘመን ሁሉ እንድታይ ያድርግህ!

6 የልጆችህን ልጆች ለማየት እንድትበቃ ያድርግህ! ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia