በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
ዘካርያስ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው” አልሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ! እነዚህ የምን ምሳሌዎች ናቸው?” ብዬ ጠየቅሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። |
በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት። እርሱም፦ እነዚህ ይሁዳንና እስራኤልን ኢየሩሳሌምንም የበተኑ ቀንዶች ናቸው ብሎ መለሰልኝ።
እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።