የብር ድሪ ሳይበጠስ፥ የወርቅም ኵስኵስት ሳይሰበር፥ ማድጋውም በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፥ ወደ መስኮት የሚያዩ ዐይኖች ሳይጠፉ፥ የአደባባይ ደጆች ሳይዘጉ፥ ስለ ቃላት ድንጋጤ ከጠላት ቃል የተነሣ የሚጮኹ ሳይነሡ፥ በአዳም ልጆች ሁሉ ወዮታ ሳይሆን፥ ወደ ላይም ሳይመለከቱ፥ በመንገድም ፍርሀት ሳይመጣ፥ እሳትም ወደ ላይ ከፍ ማለትን በወደደ ጊዜ ሳይታይ፥ በአደባባይ ልቅሶ ሳይሰማ፥ የብር መልኩ ሳይለወጥ፥ የወርቅም መልኩ ሳይጠፋ፥ መንኰራኵሩም በጕድጓድ ላይ ሳይሰበር፥