ዘካርያስ 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን፦ ከታናሽነቴ ጀምሮ ባሪያ ሆኜ ነበርሁና ገበሬ ሰው ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ ‘እኔ ገበሬ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሮዬ የተመሠረተውም በዕርሻ ላይ ነው’ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እያንዳንዱ፦ “ከታናሽነቴ ጀምሮ አገልጋይ ነበርኩ፥ መሬት አራሽ ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ገበሬ ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከወጣትነቴ ጀምሮ የእርሻ መሬት ባለቤት ነኝ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ ከታናሽነቴ ጀምሮ ባሪያ ሆኜ ነበርሁና ገበሬ ሰው ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም ይላል። |