በባዕድ ሀገር በእንግድነት በነበሩ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ዐስበዋልና፤ ምድራቸው እንስሳትን በማስገኘት ፋንታ ተቈናጣጭ ዝንብን እንዴት አወጣች? ባሕርስ በብዙው ውኃ ውስጥ በነበረው ዓሣ ፋንታ ጓጕንቸርን እንዴት አስገኘች?
በዚያን ጊዜ፥ የስደት ጉዟቸውን አስታውሱ፤ መሬት በእንስሳት ፈንታ ትንኞችን አፈራች፤ ወንዙም በአሳዎች ምትክ እልፍ አዕላፍ ዕንቁራሪቶችን ተፋ።