አሁንም ስማኝ፤ ለአባትዋም እነግረዋለሁ፤ ከራጊስም በተመለስን ጊዜ የሠርግ በዓል እናደርጋለን፤ ራጉኤል፦ በሙሴ ሕግ መሠረት ለሌላ ሰው ይሰጣት ዘንድ አይወድድምና፥ ብትሞትም በወደደ ነበር፤ከሰው ሁሉ ይልቅ ውርሷ ላንተ ይደርስሃልና።”
ከሣራ በቀር ሌላ ልጅ የለውም፥ የእርሷ የቅርብ ዘመድዋ አንተ ነህ፥ እርሷን ለማግባትና የአባትዋን ሀብት ለመውረስ ከማንም በላይ መብት ያለህ አንተ ነህ፤ እርሷም አዋቂ፥ ብርቱና መልከ መልካም ናት፥ አባትዋም በጣም ይወዳታል