ስለዚህም ለሕዝቡ የቅዱሳንን ሥርዐት ያስተምራቸው ዘንድ፥ ለእርሱና ለዘሩም ለዘለዓለም ደገኛ ክህነት ይሆን ዘንድ የሰላም ኪዳንን አጸናለት።
ከዚህም የተነሣ፥ የቤተ መቅደሱና የሕዝቡ አለቃ ሆኖ ከመመረጡመ በላይ፥ እርሱና የእርሱ ወገኖች የክህነት እልቅናን ለዘለዓለምም ያገኙ ዘንድ ቃል ኪዳንን አገኙ።