ሩት 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ። |
ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፣ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው።
በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።
ዳዊትም የዚያ የኤፍራታዊው ሰው ልጅ ነበረ፤ ያም ሰው ከቤተ ልሔም ይሁዳ ስሙም እሴይ ነበረ፤ ስምንት ልጆችም ነበሩት፤ እሴይም በሳኦል ዘመን በዕድሜ አርጅቶ ሸምግሎም ነበር።