እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም።
ሩት 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፣ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፣ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶቹ የሚያጭዱበትን ዕርሻ ልብ እያልሽ ልጃገረዶቹን ተከተዪ፤ ወንዶቹ እንዳያስቸግሩሽም አስጠንቅቄአቸዋለሁ፤ ውሃ ሲጠማሽ ደግሞ፣ እየሄድሽ ወንዶቹ ሞልተው ካስቀመጡት እንስራ ቀድተሽ ጠጪ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፥ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፥ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የት እንደሚያጭዱ በመጠባበቅ እየተመለከትሽ ከእነርሱ ጋር ሁኚ፤ ወንዶች ሠራተኞቼን እንዳያስቸግሩሽ አስጠንቅቄአቸዋለሁ፤ ውሃም በሚጠማሽ ጊዜ እነርሱ ሞልተው ወዳስቀመጡአቸው እንስራዎች እየሄድሽ ቀድተሽ ጠጪ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፤ ተከተያቸውም፤ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፤ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውሃ ጠጪ፤” አላት። |
እግዚአብሔርም በሕልም አለው፥ “ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ ዐወቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢአትን እንዳትሠራ ጠበቅሁህ፤ ስለዚህም ትቀርባት ዘንድ አልተውሁህም።
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።