ሩት 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከተቀመጠችበት ስፍራ ወጣች፣ ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ በመንገድ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኖረችበትን ስፍራ ትታ ከሁለቱ ምራቶቿ ጋራ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመልሳቸውን መንገድ ይዘው ጕዟቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከተቀመጠችበት ስፍራ ወጣች፥ ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ መንገድ ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ይሁዳ አገር ለመሄድም አብረው መጓዝ ጀመሩ፤ ነገር ግን በመንገድ ላይ ሳሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከተቀመጠችበት ስፍራ ወጣች፤ ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ በመንገድ ሄዱ። |
እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ጐበኘ እንጀራም እንደ ሰጣቸው ስለ ሰማች፥ ከሞዓብ ምድር ልትመለስ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ተነሣች።