ሮሜ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምንመካ በእርስዋ ብቻ አይደለም፤ በመከራችን ደግሞ እንመካለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕግሥትን እንደሚያመጣ እናውቃለንና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ብቻ ሳይሆን፥ መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ ስለምናውቅ በመከራም ጭምር እንመካለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ |
በዚህ ብቻ አይደለም፤ በእርሱ ይቅርታውን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም በእግዚአብሔር ዘንድ እንመካለን እንጂ።
ነገር ግን የሚተክዝ ዓለም ብቻ አይደለም፤ የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ የተቀበልነው እናም ደግሞ እናዝናለን እንጂ፤ የነፍሳችንን ድኅነት እናገኝ ዘንድ የልጅነትን ክብር ተስፋ እናደርጋለንና፤ በእምነትም ድነናልና።
ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግልባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአብያተ ክርስቲያናት ተሾመ።
ይህንም ጸጋ እግዚአብሔር ሰጥቶአችኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልትቀበሉም ነው እንጂ ልታምኑበት ብቻ አይደለም።