ሮሜ 16:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊሎሎጎስን፥ ዩልያን፥ ኔርዮስን፥ እኅቱንም አሊንጳስን ከእነርሱም ጋር ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ሰላም በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለፍሌጎን፣ ለዩልያ፣ ለኔርያና ለእኅቱ፣ እንዲሁም ለአልንጦን፣ ከእነርሱም ጋራ ላሉት ቅዱሳን ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ከእነርሱ ጋር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለፊሎሎጎስ፥ ለዩልያ፥ ለኔርያና ለእኅቱም ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እንዲሁም ለኦሉምፓስና ከእነርሱም ጋር ላሉ ምእመናን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ከእነርሱ ጋር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። |
ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ።
በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
አስቀሪጦስን፥ አልሶንጳን፥ ሄርሜስን፥ ጳጥሮባስን፥ ሄርማስን፥ ከእነርሱ ጋር ያሉ ወንድሞቻችንንም ሰላም በሉ።
ለቅዱሳንም እንደሚገባ በጌታችን ተቀበሉአት፤ እርስዋ ለብዙዎች፥ ለእኔም ረዳት ናትና፤ ለችግራችሁም በፈቀዳችሁት ቦታ መድቡአት።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥