ሮሜ 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተጻፈው ሁሉ በመታገሣችንና መጻሕፍትን በመታመናችን ተስፋችንን እናገኝ ዘንድ እና ልንማርበት ተጻፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽናትና ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን፣ ቀደም ብሎ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፏልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ነገሮች ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቅዱሳት መጻሕፍት በምናገኛቸው ትዕግሥትና መጽናናት ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብለው የተጻፉት ሁሉ ትምህርት እንዲሆኑን ተጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና። |