ሮሜ 15:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ይህን ፍሬ ጨርሼና አትሜ በእናንተ በኩል ወደ አስባንያ እሄዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሥራውን ከጨረስሁና ይህን ፍሬ መቀበላቸውን ካረጋገጥሁ በኋላ ወደ እስጳንያ እሄዳለሁ፤ እግረ መንገዴንም እናንተን አያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ይህን ፈጽሜ፥ ይህን ፍሬ ካተምሁላቸው በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ ስፔን እሄዳለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይህን የተሰበሰበውን የገንዘብ ርዳታ ወደ ኢየሩሳሌም ወስጄ የማስረከብ ሥራዬን ከፈጸምኩ በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ እስፔን እሄዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ይህን ፈጽሜ ይህን ፍሬ ካተምሁላቸው በኋላ በእናንተ በኩል አልፌ ወደ እስጳንያ እሄዳለሁ፤ |
ይህም ከተፈጸመ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚያም ከደረስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገባኛል” አለ።
ወደ አስባንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእናንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋላም ከእናንተ ወደዚያ እሄዳለሁ።
ይህም ወደ እናንተ የደረሰውን የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ከአያችሁበት ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያድግና ያፈራ ዘንድ ነው።