ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
ሮሜ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አስባንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቀደም ብዬ ከእናንተ ጋር ደስ ካለኝ በኋላም ከእናንተ ወደዚያ እሄዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ስፔን በምሄድበት ጊዜ፥ ከእናንተ ጋር ተደስቼ ጥቂት ካሳላፍሁ በኋላ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ሳልፍ ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁ ዐቅጃለሁ። ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ ብሎኝ ከቈየሁ በኋላ ጒዞዬን ለመቀጠል የሚያስችለኝን ርዳታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። |
ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
ይህም ከተፈጸመ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚያም ከደረስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገባኛል” አለ።
ከዚህም በኋላ ለመሄድ ወጣን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን።
በእናንተም በኩል ወደ መቄዶንያ እንዳልፍ፥ ዳግመኛም ከመቄዶንያ እንድመለስና እናንተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸኙኝ ዘንድ መከርሁ።