ዐዋቂዎችን ማን ያውቃቸዋል? ቃላቸውንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበራለች፥ በፊቱም ኀፍረት የሌለው ሰው ይጠላል።
ሮሜ 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ቍጣን ስለ መፍራት ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ቅጣትን በመፍራት ብቻ ሳይሆን፣ ለኅሊና ሲባል ለባለሥልጣናት መገዛት ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ስለ ቁጣው ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ይገባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ለመንግሥት ባለሥልጣኖች መታዘዝ ይገባችኋል፤ የምትታዘዙትም የእግዚአብሔርን ቊጣ ስለ መፍራታችሁ ብቻ ሳይሆን ኅሊናችሁም ስለሚወቅሳችሁ መሆን አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው። |
ዐዋቂዎችን ማን ያውቃቸዋል? ቃላቸውንስ መተርጐም የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበራለች፥ በፊቱም ኀፍረት የሌለው ሰው ይጠላል።