አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ሮሜ 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለአንተ መልካሙን ለማድረግ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ነገር ግን ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ምክንያቱም ሰይፉን በከንቱ አልታጠቀም፤ ክፉ የሚያደርገውን ለመቅጣት የቍጣ መሣሪያ የሆነ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ በከንቱ ሰይፍ አይታጠቅምና፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። |
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ፈራጆቹንም፥ “ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አትፈርዱምና፥ የፍርድም ነገር ከእናንተ ጋር ነውና የምታደርጉትን ተመልከቱ።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ፤ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
ባለ ደሙ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን በስሕተት ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት።
በማኅበሩ ፊት እስኪቆምና እስኪመረመር ድረስ ባለደሙ እንዳይገድለው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲማፀን፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ በመካካላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው።