ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ራእይ 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፤ ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፤ ከርሷ ውጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርሷ ዘንድ ውጡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላ ድምፅም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ፤ የመቅሠፍትዋም ተካፋዮች እንዳትሆኑ፤ ከእርስዋ ውጡ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤ |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
“ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ! ሂዱ፤ አትቁሙ፤ በሩቅ ያላችሁም እግዚአብሔርን አስቡ፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።