የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።
ራእይ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፤ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአውሬው ራሶች አንዱ ለሞት የሚያደርስ ቍስል ያለበት ይመስል ነበር። ነገር ግን ለሞት የሚያደርሰው ቍስሉ ዳነ፤ ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራሶቹም አንዱ ለሞት የሚያደርስ ቁስል ነበረው፤ ለሞት የሚያደርሰውም ቁስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ በመገረም አውሬውን ተከተለ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአውሬው ራሶች አንዱ ለሞት የሚያደርስ ቊስል እንደ ነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርሰው ቊስሉ ድኖአል፤ ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥ |
የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።
ፈሪሳውያንም እርስ በርሳቸው፥ “የምታገኙት ምንም ጥቅም እንደሌለ ታያላችሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከትሎታል” ተባባሉ።
ሲሞንም ወዲያውኑ አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ይከተል ጀመር፤ በፊልጶስም እጅ የሚደረገውን ተአምርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደነቅ ነበር።
በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።
በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።
እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።
ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።