የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዝአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ።
እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።
ባሕር የእርሱ ናት እርሱም ፈጠራት፥ የብስንም እጆቹ ሠሩአት።
እርሱ የፈጠረው ስለ ሆነ ባሕር የእርሱ ነው፤ የብስንም የፈጠሩ እጆቹ ናቸው።
እግዚአብሔር የዋሃንን ያነሣቸዋል፥ ኃጥአንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳቸዋል።
የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
እግዚአብሔር ከሰማይ በታች የሚታደርባቸውን ሀገሮችንና ዳርቻዎችን ሳይፈጥር።
ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።
እርሱም፥ “እኔ ዕብራዊ የእግዚአብሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።