እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና።
የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የርሱ ናቸው።
የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው።
የመሬት ጥልቀቶች በመዳፉ ውስጥ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።
እርሱ ሁሉን ቢገለብጥ፥ ምን አደረግህ? የሚለው ማን ነው?
ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትምም፤ በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።
ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አልሰማኸኝም። በሌሊትም በፊትህ አላሰብከኝም።
ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።
ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ።
ተራሮችም ከእርሱ የተነሣ ታወኩ፥ ኮረብቶችም ቀለጡ፣ ምድርና ዓለም የሚኖሩበትም ሁሉ ከፊቱ ተናወጡ።
ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።