አቤቱ፥ ኃጥኣን እስከ መቼ? ኃጥኣን እስከ መቼ ይታበያሉ?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ።
አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።
እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል።
ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።
አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።
ለርስቱ እኛን መረጠን፥ የያዕቆብን ውበት የወደደ።
ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።
እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሐሤትም ትማራላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በደስታ ሊቀበሏችሁ ይዘላሉ፤ የሜዳም ዛፎች ሁሉ በቅርንጫፎቻቸው ያጨበጭባሉ።
“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌንም አዳመጥህ።
እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።