ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
መዝሙር 91:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ ሰው አያውቅም፥ ልብ የሌለውም ይህን አያስተውለውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣ በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጨለማ ከሚጓዝ መቅሰፍት፥ በቀትር ከሚደመስስ አደጋ አትፈራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨለማ ከሚመጣ ተላላፊ በሽታና በቀትር ከሚወርድ መቅሠፍት አትሰጋም። |
ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ መጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።