ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
መዝሙር 90:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፥ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድነኛልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ “የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን ወደ አፈር ትመልሳለህ፥ “የሰው ልጆች ሆይ”፥ ተመለሱ ትላለህ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ወደነበረበት እንዲመለስ ታዛለህ፤ ተመልሶም ትቢያ እንዲሆን ታደርገዋለህ። |
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ፤ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፤ በዚያም ይሞታሉ።”