ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው በተመለሱ ጊዜ፥ ይታመሙ፥ ከፊትህም ይጥፉ።
ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣ ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤
እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
አንተ በምትገለጥበት ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ ተሰናክለውም ከፊትህ ይጠፋሉ።
እግዚአብሔር ለዘለዓለም በውኑ ይጥላልን? እንግዲህስ ይቅርታውን አይጨምርምን?
ከስንዴም ስብ አበላቸው፥ ከዓለቱም ማር አጠገባቸው።
አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዐመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
የክብርህንም ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ ተራሮች በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።
ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።