ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ተናግረሃልና አሁን እንግዲህ ለዘለዓለም በፊትህ ይሆን ዘንድ የባሪያህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘለዓለም ይባረክ።”
መዝሙር 89:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ሰዓት ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ፥ ለአገልጋዬም ለዳዊት ማልሁ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰጠኸውም የተስፋ ቃል “ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው። |
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ተናግረሃልና አሁን እንግዲህ ለዘለዓለም በፊትህ ይሆን ዘንድ የባሪያህን ቤት እባክህ ባርክ፤ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘለዓለም ይባረክ።”
እኔ፦ በእስራኤል ላይ የሚገዛ ሰውን ከአንተ አላጠፋም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።
እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፤ ልጅም ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ።
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ ይሆን ዘንድ መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሠኝ ዘንድ እኔን ሊመርጠኝ ወደደ።
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፣ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፣ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።
ኢሳይያስም ደግሞ እንዲህ ብሎአል፥ “የእሴይ ዘር ይነሣል፤ ከእርሱ የሚነሣውም ለአሕዛብ ንጉሥ ይሆናል፤ ሕዝቡም ተስፋ ያደርጉታል።”
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”