መዝሙር 84:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ምሕረቱን ይሰጣል፥ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ ሆይ! በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው! |
ጥበብን አጽኑአት፤ እግዚአብሔር እንዳይቈጣ፥ እናንተም ከጽድቅ መንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነደደች ጊዜ፥ በእርሱ የታመኑ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
ፀሐይ በቀን የሚያበራልሽ አይደለም፤ በሌሊትም ጨረቃ የሚወጣልሽ አይደለም፤ ለአንቺስ እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።