“ኑ ከሕዝብ ለይተን እናጥፋቸው፥ ከእንግዲህም ወዲህ የእስራኤልን ስም አያስቡ” አሉ።
ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።
ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፥ ከክፉዎችም እጅ አስጥሉአቸው።
ደካሞችንና ችግረኞችን አድኑ፤ ከክፉዎችም ጥቃት አስጥሉአቸው።
ድሃውን ከሚጨቁነው እጅ አድኛለሁና። ረዳት የሌለውን ደሃአደጉንም ረድቸዋለሁና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ ባልቴቲቱንም አትበድሉ፤ አታምፁባቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።