በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
መዝሙር 79:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብን በልተውታልና፤ መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብን በልተውታልና፥ መኖርያውንም ባድማ አድርገዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው። |
በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
አቤቱ፥ እጅግ አትቈጣ፤ ለዘለዓለምም ኀጢአታችንን አታስብ፤ አሁንም እባክህ፥ ወደ እኛ ተመልከት፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።
ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ አረማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው፤ ጠላቶቻቸውም፦ በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፥ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠሩ እኛ አናሳርፋቸውም አሉ።