መዝሙር 76:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድሮውን ዘመን ዐሰብሁ፤ የዘለዓለሙን ዓመታት ዐሰብሁ፤ አነበብኹም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከኀያላኑም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጀግኖች ወታደሮች የማረኩትን ተቀሙ፤ እጃቸውንም ማንሣት አቅቶአቸው የመጨረሻ እንቅልፍ አንቀላፉ |
አሦርም ይወድቃል፤ የሚወድቀውም በሰው ሰይፍ አይደለም፤ የምትበላቸውም የሰው ሰይፍ አይደለችም፤ የሚሸሹም ከሰይፍ ፊት አይደለም ጐልማሶቻቸው ግን ይሸነፋሉ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
በሞቃቸው ጊዜ እንዲዝሉ፥ የዘለዓለምም እንቅልፍ እንዲተኙ መጠጥን አጠጣቸዋለሁ፤ አሰክራቸዋለሁም፤ ከዚያም በኋላ አይነቁም፥ ይላል እግዚአብሔር።