ደነገጥሁ አልተናገርሁምም።
አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል።
በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ፥
አምላክ ሆይ አንተ አስፈሪ ነህ፤ ግርማህም ከታላላቅ ተራራዎች በላይ ነው።
አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፤ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ስማኝ።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
እርሱም በአንበሶች መካከል አደገ፤ ደቦል አንበሳም ሆነ፤ ንጥቂያም ተማረ፤ ሰዎችንም ነጥቆ በላ።
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።