መዝሙር 73:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኑ የአንተ ነው፥ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሐይንና ጨረቃን ፈጠርህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣ አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ለመረዳት ኅሊናዬን አነቃሁ፤ ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት። |
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
ከፀሓይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፤ ደግሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወቅሁ” ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም።
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።