መዝሙር 72:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዐመፀኞችን ሰላም አይቼ በኃጥኣን ላይ ቀንቼ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮች ብልጽግናን፣ ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጽድቅ፥ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተራራዎች ብልጽግናን፥ ኰረብቶችም የጽድቅ ፍሬን ለሕዝብ ያስገኙ። |
“ሰማይ በላይ ደስ ይበለው፤ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ፤ ምድርም መድኀኒትን ታብቅል፤ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ፈጥሬሃለሁ።
ሰላምን የሚያወራ፥ መልካም የምሥራችንም የሚናገር፥ መድኀኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፥ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን እሰጥሻለሁ። ለአለቆችሽም ሰላምን፥ ለመኳንንትሽም ፍርድን አደርጋለሁ፤
“በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች ማርን ያንጠባጥባሉ፤ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፤ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፤ የሰኪኖንንም ሸለቆ ታጠጣለች።