አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ ጌታዬ ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ ተስፋ አደረግሁህ።
እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴና፣ ታዳጊዬም ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።
የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ አትዘግይ!
በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ለመንሁ።
“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚመጣውም ፈጥኖ ይደርሳል፥ አይዘገይምም።
ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ!ጅ ና።