እነሆ፥ ዐመፀኛ በዐመፁ ተጨነቀ፤ ጭንቅን ፀነሰ፤ ኀጢአትንም ወለደ።
ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣ ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።
የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።
ኃጢአተኞች በደልን ይፀንሳሉ፤ ተንኰልን ያረግዛሉ፤ ውሸትን ይወልዳሉ።
የኃጥእ ሰው ዕድሜው በጭንቅ ያልፋል፥ ለግፈኛ የተመደቡ ዓመታቱም ሁሉ የተቈጠሩ ናቸው።
በሆዳቸው ጭንቅትን ይፀንሳሉ፥ ከንቱ ነገርንም ይወልዳሉ። ሆዳቸውም ተንኰልን ያዘጋጃል።”
ዛሬ ታያላችሁ፤ ዛሬ ታደንቃላችሁ፤ የመንፈሳችሁም ኀይል ከንቱ ይሆናል፤ እሳትም ትበላችኋለች።
ለመከራ እሰበስባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎችንም እጨርስባቸዋለሁ።
ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።