እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሃ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ።
አምላክ ሆይ! ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤትን ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው።
ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን” አለው።