ምድርን አናወጥሃት፥ አወክሃትም፤ ተናውጣለችና ቍስልዋን ፈወስኻት።
ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።
አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶቼ አድነኝ፥ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ።
ከነዚያ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከነዚያም ነፍሰ ገዳዮች ታደገኝ።
ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ።
በቤተ መቅደስህ እጆችን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።