እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል።
ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤
ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ፥ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብም መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
አቤቱ፥ ፈተንኸኝ፥ ዐወቅኸኝም።
አሕዛብ ለምን ዶለቱ? ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ?
አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኀኒትን ያዘዝህ።
እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ነበልባሉም ጠላቶቹን ይከብባቸዋል።
አሕዛብም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ ይቅር ብሎአቸዋልና፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ መካከል እገዛልሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።”
ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእላፍን ከሕዝብ ጋር አስነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔውንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀይል ተነሣ፤ ዲቦራም ባርቅን አጽኚው፥ የአቢኒሔም ልጅ ባርቅም ሆይ! ምርኮህን ማርክ።