በእግዚአብሔር ቃሉን አከብራለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤ የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።
ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ የተነሣ፥ ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።
ልቤ በውስጤ አስጨንቆኛል፤ የሞት ፍርሀትም ወደቀብኝ።
ሳሚም ሲረግመው እንዲህ ይል ነበር፥ “ውጣ! አንተ የደም ሰውና ዐመፀኛ ሰው ሂድ! ሂድ!
ነፍሴም እጅግ ታወከች፤ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?
ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፥ ለባሪያዬም ለዳዊት ማልሁ፥
“አሁንስ ነፍሴ ታወከች፤ ግን ምን እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍሴን አድናት፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደርሻለሁ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነበረበት ጊዜ፥ በታላቅ ጩኸትና እንባ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ጽድቁንም ሰማው።