መዝሙር 51:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥ በጻድቃንህም ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊትህን ከኀጢአቴ መልስ፤ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፥ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤ በደሌን ሁሉ ደምስስ። |
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ያጠልቀዋል፤ በቤቱም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥንቱንም ወይም የተገደለውን፥ ወይም የሞተውን፥ ወይም መቃብሩን በነካው ላይ ይረጨዋል።
ከባላጋራችን የተነሣ በትእዛዝ የተጻፈውን የዕዳችንን ደብዳቤ ደመሰሰልን፤ ከመካከላችንም አራቀው፤ በመስቀሉም ቸነከረው።